ድርጅትዎን በፌስቡክ እንዴት ማስተዋወቅ ይችላሉ?

02/03/2019

ለንግድዎ የፌስቡክ ገጽ አዘጋጅተዋል? በጣም ጥሩ! ቀጥሎስ ምን ማድረግ ይኖርብዎታል?


በፌስቡክ ገጽዎ ተከታይ ከሆኑና ካልሆኑ ደንበኞች ጋር መገናኘት ለመጀመርና ማስታወቂያዎን ለማዳረስ በመጀመሪያ ማድረግ ያለብዎት ጥቂት ነገሮች አሉ። የፌስቡክ ገጽዎን ለማስተዋወቅና ከደንበኞችዎ ጋር እንዴት መገናኘት እንደሚችሉጥቂት መንገዶች እንጠቁምዎት።


1. ያለዎትን ግንኙነቶች (የትውውቅ መስመር) መጠቀም

በዙሪያዎ የሚገኙ ደንበኛ የመሆን አቅም ያላቸውን ሰዎች ኢሜል አድራሻ በመሰብሰብ የኢሜል ካምፔን ማዘጋጀት። አንድ ሰው የኢሜል ዝርዝርዎን ከተቀላቀለ በፌስቡክም ከእርስዎ ጋር የመገናኘት እድሉ ሰፊ ነው። የፌስቡክ ሊንክዎንና የተሰማሩበትን የንግድ ዘርፍ በኢሜል ይላኩ፣ አዲሱን ገጽዎን ያሳውቁ እና ሰዎች በፌስቡክ ላይ ገጽዎን እንዲከተሉ ይጋብዙ። እንዲሁም በኢሜልዎ ግርጌ ላይ ማህበራዊ ሚዲያ አዝራሮችን (icons) ቢያስቀምጡ ኢሜይል የላኩላቸው ሰዎች በቀላሉ ገጽዎን እንዲያገኙት ይረዳል።


2. በድረገጽዎ ላይ የፌስቡክ ላይክ ቁልፍ ማስቀመጥ

ለድረገጽዎ ጎብኝዎች በድረገጽዎ ወይም በብሎግዎ ላይ የተካተተ የፌስቡክ ላይክ ቁልፍን በመጨመር ገጽዎን እንዲከተሉ አማራጭ ያቅርቡላቸው።


3. የፌስቡክ ማስታወቂያ መልቀቅ

ፌስቡክ ማስታወቂያዎን በመልቀቅ ገጽዎን ከአዲስ ታዳሚዎች ጋር ለማስተዋወቅና ተከታዮች ለመጨመር እጅግ ቀላሉ መንገድ አለው። የፌስቡክ ተጠቃሚዎችን በዕድሜ፣ በጾታ፣ በመኖሪያ አካባቢና በፍላጎት በመለያየት ሊደርሱ የሚፈልጉትን የደንበኛ አይነት መምረጥ ማስታወቂያው ለመረጡት አይነት ተጠቃሚ ብቻ እንዲደርስ ማድረግ ይችላሉ። ይህን ለማድረግ የሚከፈለው ክፍያም በቀን ከ5 የዩኤስ ዶላር ጀምሮ ሲሆን በዚህም ክፍያ እንደየ አካባቢው ተጠቃሚ ሁኔታ ከ5000 ያላነሰ ሰው በየቀኑ መድረስ ይችላሉ። ይህን አገልግሎት ለመጠቀም ከፈለጉ Wazema.net ላይ ያግኙን።


4. ተመልካች የሚያበዙ አጋዥ ይዘቶችን ማጋራት

በማኅበራዊ ሚዲያ እና ማኅበራዊ ሚዲያን በማስተዋወቅ ሽያጭ መፍጠር መካከል ትልቅ ልዩነት አለ። ከቢዝነስዎ ባለፈ ለተጠቃሚዎችዎ አጋዥ ይዘት ያላቸውን መረጃዎች በማጋራት እና እርዳታ የሚያገኙበትን መንገድ በመፍጠር ሰዎች ገጽዎን ይበልጥ እንዲወድዱት ምክንያት ይስጡዋቸው።ፌስቡክ እይታን መሰረት ያደረገ ደንበኞች የማግኛ መንገድ በመሆኑ በሚችሉት መንገድ ሁሉ ጠቃሚ ምስሎችን እና ቪዲዮዎችን ያጋሩ። ተከታዮችዎን ለማሳተፍ የሚረዱ የጥያቄና መልስ ውድድርም መሞከር ይችላሉ።


5. ገጽዎን ከOnline ውጪ ማስተዋወቅ

የቢዝነስ ካርዶችዎን፣ ምናሌዎችን (menus)፣ በራሪ ወረቀቶችን፣ ምልክቶችን፣ ቲሸርቶችን ጨምሮ በሁሉም የህትመት ግብይት ቁሳቁሶችዎ ላይ የፌስቡክ ገጽዎን ያስተዋውቁ። ወርክሾፕ፣ ሴሚናር ወይም ኮንፈረንስ ሲሳተፉ የፌስቡክ ገጽዎን ይጥቀሱ። በጠረጴዛዎ ላይ የፌስቡክ ገጽዎን የያዘ QR ኮድ አሳትመው በማስቀመጥ በአካል ያገኙት ደንበኛ የፌስቡክ ገጽዎ ተከታይ እንዲሆን በመጋበዝ አዲስ ምርት ሲኖርዎት ለዚያ ደንበኛ በቀላሉ ማሳወቅ ይችላሉ።


6. አሁን ያለዎትን ማህበራዊ ተከታዮች አለመርሳት

እንደ Telegram፣ Twitter፣ ወይም LinkedIn ባሉ ሌሎች ማህበራዊ ሚዲያ ጣቢያዎች ላይ ንቁ ተሳታፊ ከሆኑ በእነኚህ መስመሮች ላይ ገጽዎን ያስተዋውቁ። በእነኚህ መስመሮች የሚከተሉዎት ሰዎች በፌስቡክም ላይ ከንግድዎ ጋር ለመገናኘት ደስተኞች ይሆናሉ።


አሁን የፌስቡክ ገጽዎን ለማስተዋወቅ ዝግጁ ነዎት?


የፌስቡክ ገጽ እንዳለዎት ማንም የማያውቅ ከሆነ ምን ጥቅም አለው? ተከታዮችዎን ለመጨመር እና ከማህበራዊ አውታረመረቦች ጋር እውነተኛ ተጽዕኖ ለማሳደር በሚችሉበት ቦታ ሁሉ ገጽዎን ያስተዋውቁ። ለበለጠ መረጃ Wazema.net ላይ ያግኙን።