በዩቲዩብ ቻነል እንዴት ገንዘብ መስራት ይችላሉ?

11/08/2019

ከአንድ ቢሊዮን በላይ ተጠቃሚዎች፣ በየቀኑ የአንድ ቢሊዮን ሰዓታት ቪዲዮ ዕይታዎችና እና በየደቂቃው ከ400 ሰዓታት በላይ ቪዲዮዎች የሚሰቀሉበት (upload የሚደረጉበት) ዩቲዩብ፣ ተጠቃሚዎቹ በቪዲዮዎቻቸው ገንዘብ የሚያገኙበት ጥሩ መንገድ ያለው መድረክ (platform) ነው። በዩቲዩብ ገንዘብ ለመስራት የባለሙያ እገዛም ሆነ ውድ መሣሪያ አያስፈልግዎትም (በቂ ጥራት ያለው ቪዲዮና ድምፅ በሞባይል ስልክዎ መቀረጽ ይችላሉ)።


በዚህ ጽሑፍ ውስጥ በዩቲዩብ ቪዲዮ ገንዘብ ማግኘት የሚችሉባቸውን ቀላል መንገዶችን እንጠቁምዎታለን።


1. በማስታወቂያ አማካኝነት (Ad Revenue)

ቪዲዮ ወደ ዩቲዩብ ሲሰቅሉና የእርስዎን ቪዲዮ ያጫወተ ሰው በየመሃሉ ማስታወቂያ ሲተላለፍለት ገንዘብ የማግኘት እድል ይኖርዎታል። ያስታውሱ፥ የonline ማስታወቂያዎች ንጉስ የሆነው ጉግል የዩቲዩብ ባለቤት መሆኑን።


አንድ ሰው ቪዲዮዎ ከመጀመሩ በፊትም ሆነ ከጀመረ በዃላ ከሚታዩት በአንዱ ማስታወቂያዎች ላይ ጠቅ ሲያደርግ ዩቲዩብ ገንዘብ ይከፍልዎታል። እነዚህ ዓይነቶች ማስታወቂያዎች ሲ.ፒ.ሲ (CPC: cost per click) ተብለው ይጠራሉ፥ ይህም ማለት አስተዋዋቂው በጠቅታው ልክ እንዲከፍል እና ዩቲዩብ እና እርስዎ የማስታወቂያውን ክፍያ ይጋራሉ ማለት ነው። ተከፋይ ሊሆኑ የሚችሉበት ሌላኛው መንገድ ደግሞ አንድ ሰው በቀላሉ ያለምንም (ጠቅታ) click በቪዲዮዎችዎ ላይ ማስታወቂያዎችን ከተመለከተ ነው። ይህኛው ሲ.ፒ.ኤም (CPM: cost per mile) የሚባል ሲሆን ለእያንዳንዱ 1000 የማስታወቂያ እይታ የተወሰነ መጠን ይከፈለዎታል ማለት ነው።


ታዲያ ክፍያዎትን ለመሰብሰብ በዩቲዩብ እና በ Google የማስታወቂያ ስርዓት (Google AdScense) ስርዓት ውስጥ መመዝገብ ይኖርብዎታል። ይህም ከመደበኛው የዩቲዩብ መለያዎ ውጪ ነው። ቀጥሎም የገቢ መፍጠሪያ (monetization) አማራጭ በማብራት የYouTube መለያዎን ከጉግል አድሴንስ መለያ ጋር ያገናኛሉ።


አሁን በዩቲዩብ ቪዲዮዎች ገንዘብ ማግኘት ለመጀመር ዝግጁ ነዎት። ታዲያ ገንዘቡ የሚጠራቀምበት ቋት (ክሬዲት/ዴቢት አካውንት ያስፈልግዎታል)። ለአካውንት አከፋፈት መረጃ ይህን ሊንክ ተጭነው ጥያቄዎትን ያቅርቡልን።


2. በቀጥተኛ የምርት ትውውቅ አማካኝነት

ይህ Product Placement በመባል የሚታወቅ የማስታወቂያ አይነት ሲሆን በዩቲዩብ ላይ ገንዘብ ለማግኘት ሌላኛው መንገድ ነው። ለምሳሌ የውበት አጠባበቅ ጣቢያ ካለዎት፥ ከርሊንግ ብረት ወይም ብሩሾችን የሚያመርት ኩባንያ ምርቶቻቸውን እንዲጠቀሙ እና ለተመልካቾችዎ እንዲመክሯቸው ፍላጎት ሊኖረው ይችላል። ከኩባንያው ጋር በሚኖርዎት ስምምነት ላይ በመመርኮዝ በቪዲዮዎችዎ ስር ባሉ ሊንኮች በኩል ከተሸጡት ምርቶች ውስጥ በመቶኛ ወይም ደግሞ በቪዲዮዎ ውስጥ ያለውን ምርት በማሳየትዎ ብቻ  የተወሰነ መጠን ሊከፈሉ ይችላሉ። በዩቲዩብ ቪዲዮዎችዎ ውስጥ ከስፖንሰሮች ጋር ሊያደርጉዋቸው የሚችሏቸው ብዙ የተለያዩ ዓይነቶች ስምምነቶች አሉ።


Google በሚተዳደርበት የፌዴራል ንግድ ኮሚሽን ደንብ መሠረት አንድ ምርት የሚያስተዋውቁ ከሆነ ስለእሱ ግልጽ መሆን አለብዎት። በYouTube ዳሽቦርድዎ ውስጥ “የተከፈለ ማስተዋወቂያ” ሳጥን ላይ ጠቅ እንዲያደርጉ ይገደዳሉ።


3. የYouTube Red ምዝገባ ቻነሎች

የዩቲዩብ ከማስታወቂያ-ነፃ የደንበኝነት ምዝገባ መድረክ  (ዩቲዩብ ሬድ) ገቢን ለማምጣት ሌላኛው መንገድ ነው። ቻነልዎ ከ1000 በላይ ንቁ ተመዝጋቢዎች ካሉት፥ ዩቲዩብ ሬድ ተመልካቾች ይዘትዎን እንዲያዩ የሚያስከፍልበት እና beLive-Stream በሚደረጉ ውይይቶች ወቅትም ልዩ ክፍያ የሚቀበሉበትን አማራጭ ያቀርባል።


እነዚህ ፕሪሚየም አማራጮች ዕድሜያቸው 18 ዓመትና ከዚያ በላይ ለሆኑት ለቲዩብሪዎች ብቻ ያገለግላሉ።


4. በጣቢያዎ ላይ ምን ማሳየት አለብዎት

ከፍተኛዎቹ ተከፋይ የዩቲዩብ ቻናሎች በመቶዎች የሚቆጠሩ ካነሰም ደግሞ በደርዘን የሚቆጠሩ ቪዲዮዎች አላቸው። ብዙ ቪዲዮዎች —> የተሻሉ እይታዎች —> በርካታ ማስታወቂያዎች —> በርከት ያለ ገንዘብ! በዓለም ላይ ያሉ ምርጥ የዩቲዩብ ጣቢያዎች ሁሉንም ዓይነት ልዩ ልዩ ገበያዎች ይሸፍናሉ፥ ስለሆነም ከፍላጎቶችዎ በአንዱ በዩቲዩብ የሚከፈሉበት ጥሩ አጋጣሚ አለ።


5. ትርፋማ የሆነ ገበያ ይምረጡ

የሚመርጡት የዩቲዩብ ቻነል ይዘት ተፈላጊና ተመልካች ሊኖረው የሚችል መሆኑን በቅድሚያ ያጣሩ። በእርግጥ ሁሉም ይዘቶች የራሳቸው ተመልካች መደብ ቢኖራቸውም በቀላሉ ያለብዙ ልፋት የሚታዩ የቪዲዮ ይዘቶች እንዳሉ አይዘንጉ።